Sunday, August 18, 2013

በመንፈስ መጸለይ



በመንፈስ መጸለይ

በጭንቀትና በሀዘን ውስጥ ወይም ግራ በሚገባ ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንዴት እንደምንጸልይ አናውቅም፡፡አንዳንዴም የምናወጣቸው ቃላቶች እና አእምሮአችን ልንጸልይ የምንፈልገውን መግለጽ ሊያቅታቸው ይችላል፡፡ቃላት ጸሎታችንን መግለጽ ሲያቅተው በመንፈስ ቅዱስ ላይ በመደገፍ እርሱ በውስጣችን እንዲቃትት ብንፈቅድለት ከፍ ያለ ጸሎት መጸለይ እንችላለን፡፡ሮሜ 26-27


ብዙ የስነ-መለኮት አዋቂዎች ሀና በመንፈስ ትጸልይ እንደነበረ ይስማማሉ፡፡(1ሳሙ 112-16)ከንፈሯ ይንቀሳቀስ ነበር ነገር ግን ድምጽዋ አይሰማም ነበር፡፡ስለዚህ ታላቁ የእግዚአብሄር ሰው ኤሊ ተሳስቶ ጠጥታ የሰከረች መሰለው፡፡ሀና ከበድ ባለ ጭንቀት ውስጥ ስለ ነበረች በመንፈስ ትቃትት ነበር፡፡ሃና በአራቱም ማእዘን እየደረሰባት ካለው ፈተና የተነሳ ምሬት ውስጥ ነበረች፡፡በሴትነቷ እና በሚስትነት ማንነቷ ላይ የተነጣጠረ አደጋ ስለነበረ ነው መከራዋን ከበድ ያደረገው፡፡ስለዚህም እግዚአብሄርን በጽኑ ፈለገችው፡፡በመንፈስ ብርቱ ጸሎትን ጸለየች፡፡በዘመኑ ብርቱ የነበረ ሳሙኤልን ወለደች፡፡


እኛም አዳጋች ነገር ሲገጥመን ወደ ጸጋው ዙፋን መጥተን በመንፈስ ብንጸልይና ረዘም ላሉ ሰአታት ብንቃትት ጸሎቱ በቀጥታ ከእግዚአብሄር ጋር ስለሚያገናኘን እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ያለ ጸሎትን እንጸልያለን፡፡ችግራችንም በእግዚአብሄር ጊዜ ይንከባለላል፡፡

እግዚአብሄር ሆይ እባክህ የጸሎትን ሚስጥር ግለጥልን!

                        



Friday, August 16, 2013

ልዩ ነህ



     ልዩ ነህ

ውበትህ ልዩ ነው
    የለም የሚመስልህ
አሰራርህ ልዩ
   ብዙ ነው ጥበብህ
ሰምቼ ነበረ ብዙ በጆሮዬ
አይኔ አይታሀለች
      የኔም በተራዬ
ታዲያ ለማሞገስ
ቃላት አጣሁና
      አንተ ለማወደስ
ዝም ብዬ ብዳክር
የሚመጥን ሀሳብ
    ቢጠፋኝ ብቸገር
እንዲያው ሁሉን ጥዬ
እጆቼን አነሳሁ
    ፊቴን አንጋጥጬ
    ይገባሃል ብዬ!