Saturday, August 10, 2013

ጌታ ሆይ ተገለጥ



ጌታ ሆይ ተገለጥ

እባክህ ጌታ ሆይ
       ስማን እሺ በለን
እሳትህን ጣለው በመካከላችን
በረዶው ሰለቸን ከቦን በዙሪያችን
በግምባር ተደፍተው
              በውነት ያመለኩህ
ክብርህን አይተው ነው
               የተዋረዱልህ
ስለዚህ ተገለጥ
            ተገኝተህ ገላግለን
መሮናል እሳቱ ሰዎች የለኮሱት
            ቅንጣትም አልበጀን !


መዝ 85፡6
አቤቱ ትመለሳለህ ታድነንማለህ
ህዝብህም በአንተ ደስ ይላቸዋል


 

No comments:

Post a Comment