ለጌታ ሊኖረን የሚገባ በቂ ምላሽ
መሀልይ 5፡1-6
በዚህ ምእራፍ ውስጥ ያለችው ተዋናይ ሴት ስለውዷ በቂ እውቀት የነበራት ሴት ስትሆን ሊጎበኛት ሲመጣ
-በቂ ምላሽ ለመስጠት ዘገየች
-አጥጋቢ ምላሽን ባለመስጠቷ ውዷ ጥሏት ሄደ
-ከዚህም የተነሳ የደረሰባትን መከራ እናያለን
ለዚች ባለእድል ሴት የቀረበው ግብዣን መሀ 5፡1 ላይ እናገኘዋለን፡፡እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹እስክትረኪ ድረስ ጠጪ››
ከዚህ አውደ ንባብ የምንረዳው አንድ ነገር አለ፡፡ውዷ ወደ ዚች ሴት የመጣበት ምክንያት ጠጥታ እንድትረካ ነው፡፡በእኛም ህይወት የጌታ ከፍ ያለው ሃሳብ ከእርሱ ጋር ከሚኖረን ህብረት የተነሳ ስለምናገኘው ህብረት እና እርካታ ነው፡፡ይህም እረፍትና እርካታ በህይወታችን ሲኖር ጠንካራና የሚታይ ምስክርነት ይኖረዋል፡፡
እብራውያን 4፡10-11 ላይ ‹‹ስለዚህ ያንን ትውልድ ተቆጥቼ ፡-ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ እንዲሁ ፡-ወደ እረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ፡፡››የሚል ቃል ገራሚ ቃል አለ፡፡የጌታችን የልብ ሀሳብ ለህይወታችን መልካም ሆኖ ሳለ ብዙ ጊዜ ልቤ ሲያፈነግጥና፣ሳስቸግረው እና ስንጋደድ እራሴን አገኘዋለሁ፡፡ማለትም የኔ ህይወት ከዚች ሴት ምላሽ ጋር በሚገባ ይመሳሰላል፡፡
ዮሀንስ 10፡10 ላይ እኔ ህይወት እንዲሆናችሁ እንዲበዛላችሁ መጣሁ ይላል፡፡ማለትም ህይወቱ በዝቶልን ለሌሎች እንድንተርፍ ነው የጌታ ዋና የልብ ሀሳብ!
ግን እንደምታዘበው ከኔም ሆነ ከብዙዎች ክርስትያኖች በቂ ምላሽ እያገኘ አይደለም፡፡ብዙ ነገሮችን በቀለም ደረጃ እናውቃለን፡፡ግን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ፡-
ጌታን በሚገባ በግል እናውቀዋለን ወይ ?
ህይወቱ በዝቶልናል ወይ ?እረክተናል ወይ ?
ከዚህ የተነሳ ሰዎች በእኛ ህይወት ክርስቶስን እያዩ ነው ወይ ?
No comments:
Post a Comment