ጎበዝ እንገኝለት
እግዚአብሄር ሊባርከንና ሊያስደንቀን ይፈልጋል፡፡ግን ጌታ ከእኛ በቂ ጊዜን ይፈልጋል፡፡ብዙ ጽሞና፣ብዙ
ፊቱን መፈለግ፣ብዙ መቃተት እና በእግሩ ስር መሆን ያስፈልገናል፡፡መዝ 89፡20-21 ስንገኝለት ስላለ በረከት ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት
ቅዱሱን ዘይትም ቀባሁት
እጄም ትረዳዋለች
ክንዴም ታጸናዋለች
ባጭሩ ሶስት በአእምሮ ለመረዳት የሚከብዱ ድንቅ በረከቶችን እናገኛለን፡-
1.የመንፈስ ቅዱስ ቅባት በሀይል ወደ ህይወታችን ይመጣል
2.እርዳታውና ሞገሱ በህይወታችን በሚታይ ሁኔታ ይበዛል
3.መረጋጋትና ጽናት የህይወታችን መገለጫ ይሆናል
እነዚህ ከላይ ያሉ በረከቶች በነካ ነካ ጸሎት አይመጡም ፡፡የጸሎት ጀግኖች መሆን አለብን፤በጸጋው
ዙፋን ፊት አብዝተን መሆን ይጠበቅብናል፡፡እንደ ጳውሎስ እና እንደ ኤጳፍራ የጸሎት ሰዎች መሆን ያስፈልገናል፡፡ያኔ ለብዙ ሰዎች
የምንጠቅም የጌታ ባሪያና የክብር እቃ እንሆናለን፡፡ጌታ ሆይ ያለ መታከት ፊትህን እንድንፈልግ እርዳን!
No comments:
Post a Comment