ህዝቤ ሰምቶኝ ቢሆን
የጌታን ድምጽ ሰምቶ መራመድ ስኬታማ እንደሚያደርግ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡የጌታን
ድምጽ ደግሞ በተለያዩ መንገዶች እንሰማለን፡፡ለምሳሌ፡-
· ቃሉን ስናነብ
· ስንጸልይ
· ከነቢያት፣ከአስተማሪዎች እና ከሰባኪዎች
· በህልም ወዘተ
በህይወታችን የጌታ ምሪት እንዲበዛ ከእርሱ ጋር ያለን ህብረት እያደገና
እየጠለቀ መምጣት አለበት፡፡ለዚህ ስኬት ደግሞ በእግሩ ስር እንደ ማርያም መገኘት ምርጫ ያለው ጉዳይ አይደለም፡፡መዝ 81፡13-16
የጌታን ድምጽ ሰምቶ ስለመራመድና በመንገዱ መሄድ ስላለው በረከትና ጥቅም ዘርዘር ተደርጎ ተቀምጧል፡፡ይህ ክፍል ያስደንቀኛል፡፡ከዚህ
ቃል አንጻር ህይወቴን ሳየው እጅግ ያሳዝነኛል፡፡የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝ አለው ደግሞ በመታዘዝ ቃሉን ስንተገብር የሚመጣ በረከት
አለ፡፡
ትእዛዝ------------------------›በረከት (ትልቅ መርህ)
ከላይ የጠቀስኩት ቃል ላይ ትእዛዞቹ ሁለት ናቸው፡-
· ህዝቤ ሰምቶኝ ቢሆን
· እስራኤል በመንገዴ
ሄደው ቢሆን
በረከቶቹን በእራሴ እይታ ጠቅለል አድርጌ በሶስት አስቀምጫቸዋለሁ፡-
1.የጠላቶቻችን መሸነፍና መዋረድ
2.የረጅም ዘመን መንፈሳዊና አካላዊ ጤንነት
3.ከጌታ ጋር ከሚኖረን ህብረት የምናገኘው ከአእምሮ የሚያልፍ ጉብኝት(ከአለቱ
ማር መጥገባችንና ከስንዴው ስብ መብላታችን የሚለው ሀሳብ ይህንን ያሳያል)
ይሄ ቃል ልካችን ነው፡፡ወደዚህ ቃል ልክ ለማደግና ድምጹን በመስማት
የሚገኘውን በረከት ለመካፈል ደግሞ
· ቃሉን መብላት ማሰላሰል
እናም ባልተከፋፈለ ልብ ማጥናት ያስፈልገናል
· ጠበቅ ያሉ መንፈሳዊ
ጸሎቶችን ማድረግ ይጠበቅብናል
· ጾምን መለማመድ በጣም ጠቃሚ
ነው
እንዲህ ብናደርግ እርግጠኛ ነኝ ህይወታችን ካሰብነው በላይ ይባረካል፡፡
ጸሎት ፡-ጌታ ሆይ ድምጽህን ሰምተን እንድንራመድ እርዳን!
No comments:
Post a Comment